Psalms 87

ጽዮን የሕዝቦች እናት

የቆሬ ልጆች መዝሙር፤ ማሕሌት።

1መሠረቱን በተቀደሱ ተራሮች አቆመ፤
2 እግዚአብሔር ከያዕቆብ ማደሪያዎች ሁሉ ይልቅ፣
የጽዮንን ደጆች ይወድዳል።

3የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፤
ስለ አንቺ ክቡር የሆነ ነገር እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ ሴላ
4“ከሚያውቁኝ መካከል፣
ረዓብንና
የግብፅ ቅኔያዊ ስያሜ ነው።
ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤
እነሆ፤ ፍልስጥኤምና ጢሮስ ከኢትዮጵያ ጋር፣
ወይም ረዓብ ባቢሎን፣ ፍልስጥኤምና ኢትዮጵያ

‘ይህ ሰው በዚያ ነው የተወለደው’ ይላሉ።”
5በርግጥም ስለ ጽዮን፣
“ይህም ያም ሰው በእርሷ ውስጥ ተወለዱ፤
ልዑልም ራሱ ያጸናታል” ይባላል።
6 እግዚአብሔር ሕዝቡን ሲመዘግብ፣
“ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው” ብሎ ይጽፋል። ሴላ

7የሚያዜሙም መሣሪያ የሚጫወቱም፣
“ምንጩ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛል” ይላሉ።
Copyright information for AmhNASV